ሳስበው

ሰዎች ርኅራኄ እንዲያሳዩ ወይም ሥነ ምግባር እንዲኖራቸው ለማስተማር የግድ አንድ ሳንቲም ማውጣት አያስፈልገንም ነበር። ይህን ችሎታ ለማዳበር የሚያስችል ተፈጥሮ አለው ፥ በዚህ አቅምም ነው የተፈጠረው። ይሁን እንጂ ዛሬ ያለን የዕለት ተዕለት ሕይወት ዛሬ ያለንበት የእለት ተእለት ኑሮ የተሻሉ ልብሶችን በመግዛት ፣ የተሻሉ ስሞች ፣ የተሻሉ ግንኙነቶች ፣ የተሻሉ ጉብኝቶች ፣ የተሻሉ ነገሮች በመያዝ ፣ ይህንን […]

ሳስበው

ሰዎች ርኅራኄ እንዲያሳዩ ወይም ሥነ ምግባር እንዲኖራቸው ለማስተማር የግድ አንድ ሳንቲም ማውጣት አያስፈልገንም ነበር። ይህን ችሎታ ለማዳበር የሚያስችል ተፈጥሮ አለው ፥ በዚህ አቅምም ነው የተፈጠረው። ይሁን እንጂ ዛሬ ያለን የዕለት ተዕለት ሕይወት ዛሬ ያለንበት የእለት ተእለት ኑሮ የተሻሉ ልብሶችን በመግዛት ፣ የተሻሉ ስሞች ፣ የተሻሉ ግንኙነቶች ፣ የተሻሉ ጉብኝቶች ፣ የተሻሉ ነገሮች በመያዝ ፣ ይህንን የራስ ወዳድነት ስሜት ለመጠበቅ፥ ለማስጌጥ እና ለማስዋብ  ሁሉም ሰው በየእለቱ እንዲጠፋ እየገፋፋ ይገኛል።

እውነት ነው፣ የማያጠያይቅ እና ዘላቂ ደስታ፣ ተቃራኒ የሌለው ደስታ የሚመጣው ሁሉንም እና ሁላችንም በሚያዋህድ ከፍተኛው ንቃተ ህሊና ነው። በመጻሕፍት ወይም በቪዲዮዎች አማካኝነት ለአፍታ ብቅ የሚለው ወይም በምናገኛቸው ነገሮች ላይ ተመሥርቶ የምናገኘው ደስታ አይደለም ።

ስብዕና እያንዳንዱን ሰው በቀለም፣ ቅርፅ፣ ስነ-ልቦናዊ ደረጃ እንደ ለራስ ከፍ ያለ ግምት፣ የፋይናንስ ደረጃ፣ ስልጣን፣ ውበት፣ ተሰጥኦ፣ ወዘተ በሚለዩት በተወሰኑ ድንበሮች እራሱን እንዲገለጽ ውሱን የሆነ ስሜት ውስጥ እንዲገባ አድርጓል።

የባሕርይ ልዩነት መኖሩ ስህተት ባይሆንም ሕይወትን ሙሉ በሙሉ የመምራት እና በተሟላ ሁኔታ የመለማመድ  አቅማችንን በእጅጉ ይገድበዋል ። ምክንያቱም በዚህ የግለሰብነት ስሜት ህይወት ላይ ስላጋጠመኝ በትንንሽ ስኬቶች እና ውድቀቶች ብቻ በመመራት ሌሎች እዚያ ያለውን እና ያሉትን ሁሉንም ነገር አያካትትም ስለሆነም አብዛኛውን ጊዜ በሌሎች ኪሳራ ወይም ውደቀት እንድንደሰት ይሆናል። ስለዚህም ነው እራሳችንን በጦርነት እና በማያባራ ግጭት ውስጥ የምናገኘው።

ሁላችንም በሥጋዊ አካላችን ውስጥ እና አዕምሮችን ልዩ ባሕርያት እንዳሉን ፥ በአእምሯችን ውስጥ የሚዞሩትን እና በእለት ተእለት ሕይወታችን የሚያጋጥሙንን ነገሮች ሙሉ በሙሉ እንዲሆን እንደምንፈልገው የመቆጣጠር ኣቅማችን ውሱን ነው። ይሁን እንጂ፣ ሰው የመሆን ከፍተኛው እና ንጹህ ጥራት ያለው ባሕርይ ከላይ እንደጠቀስነው በሸማቾች ዓለም ውስጥ ሳይሆን በሌላ ነገር ላይ ያርፋል። ይህም ሙሉ በሙሉ ልዩ ያልሆነ ነገር ግን ለሁሉም አንድ እና ተመሳሳይ የሆነው ንቃተ ህሊና ነው። 

ዓለምን እና በውስጧ እየሆነ ያለውን ነገር ስለራሳችን እውነታዎች የምናውቅበት ሂደት ነው። ይህ ንቃት እና ግንዛቤ የፍቅርን፣ የይቅርታን፣ ስሜት መረዳትንና፥ የርህራሄን፣ የመረዳዳትን፣ ሌላውን ማቀፍ እና በማንኛውም ሁኔታ ደስተኛ ህልውናን እንዲኖረን የሚያነሳሳ ነው። ኣሉን የምንላችው ከስሳሙ ኣለም ያዳበርነው የሰውነታችንና የአእምሯችን ባሕርያት ከዚህ ዓለም ውጪ ያሉ የሚመስሉ እነዚህን ልዩ ነገሮች ማምጣት በፍጹም አይችሉም። ዓለማችን እነዚህን ባሕርያት ማሳየት የምትችል አይደለችም ፤ ነገር ግን እነዚህ ባሕርያት የሚወለዱት አንድ ሰው ስለ ራሱ ማንነት ለማወቅ በመምረጡ ምክንያት ከአካላዊ ወይም ከአዕምሮአዊ ብቻ ወደ ሌላ ንቃተ ህሊና ለመውጣት ሲወስን\ስትወስን ነው ።

እናንትስ ምን ይመስላቹል?